በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች የንጹሀን ዜጎች ጭፍጨፋ መጠኑም ሆነ የጭካኔው ደርጃ እየከፋ መምጣቱ ከማሳሰብ አልፎ የዜጎችን ውሎ ማደር ጥያቄ ወስጥ በማስገባት ላይ የገኛል። የዜጎች ህይወት በተለይም የሙስሊሞች ህይወት የየአከባቢው ፅንፈኛ ቀዳሚ ኢላማ ከመሆን ባሻግር ለፖለቲካም ሆነ ለዘር ጥላቻ የሙስሊም እናቶችና ህፃናት ደም ካልጎረፈ ወይም የሙስሊሙ መስጂዶችና ንብረት ካልወደመ የማይሳካላቸው ይመስላል ።
ሰሞኑን ሰዎችን እንዳሻቸው ከቤታቸው ጎትተው ወይም ከመኪና አውርደው በማናለብኝነት ሲረሽኑ አይተን ከሀዝን ድባብ ሳንወጣ በጊምቢ ዞን ቶለ ወረዳ ለበርካታ አስርት ዓመታት ከአከባቢው ሀዝብ ጋር ተዋደውና በሰላም ይኖሩ የነበሩትን ሙስሊሞች ጽንፈኛ ኃይሎች ብሄርንና ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ከህፃን እስክ ሽማግሌ ሳይለዩ በፈጸሙት አሳዛኝና አሰቃቂ የጀምላ ግድያ የበርካታ ሰዎች ህይዎት መጥፋቱና መሳጂዶች ሳይቀሩ ነፍሳቸውን ለማዳን በተጠለሉ ሙስሊሞች ደም መጭቅየቱ ልብ ይሰብራል። ድርጊቱ ባጋጣሚ የተፈጠረ ሳይሆን በወለጋ በተለያየ አከባቢ ከሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች የሙስሊሙ ማህበረሠብ አከባቢ ብቻ ተመርጦ ባለፉት አራት ዓመታት በተደጋጋሚ ጥቃት ሲደርስበትና ሲፈናቅል የቆየ ነው::
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር በሲያትል (ኢማስ) ይህንን አሰቃቂ ብሄርና ሀይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ በጥብቅ የሚያወግዝና በደረሰዉ ጥቃት ከልብ ያዘንን መሆኑን እያስታወቅን ማንኛውም በቀጠናው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ሀይል በህፃናትና በእናቶች ደም የሚገኝ የፖለቲካ ተርፍ እንደማይኖርና የተሳሳት ስሌት መሆኑን ተገንዝቦ ከሙስሊሞች ላይ እጁን እንዲሰበስብ እናሳሰባለን። መንግስትም የዜጎች ሠላምና ደህነት መጠበቅ ገዴታው መሆኑን አውቆ ቅድሚያ እንዲሰጥና ወንጀለኞችን አድኖ ለፍርድ እንዲያቀርብ አበክረን እንጠይቃለን።
በመጭረሻም የኢማስ ቦርድና ሰራ አስፍጻሚ በኢማስ ኮሚኒቲ ስም የሞቱትን አላህ ሸሂድ እንዲያደርጋቸውና ቤተሰቦቻቸውንም አላህ ሰብር እንዲሰጣቸው እየተማጸንን ወደፊት ለሚደረገው ማንኛውም እገዛ ከጎናቸው የምንቆም መሆናቸንን እናርጋግጣለን።
Leave Your Comments