;
بسم الله الرحمن الرحيم

 

  O men! Certainly the promise of Allah is true. Let not then this present life deceive you. nor let the Chief Deceiver deceive you about Allah. [Fatir 35:5] አላህ ዋክብር!  አላህ ዋክብር!  አላህ ዋክብር
  

 

በ05/05/2012 ከደሴ  የተላለፈውን የBBN  ሙሉ ዘገባ ያዳመጡ ታሪኮንም ይወቁ 

   

 

ከኮሚቴ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ግንቦት 2፣ 2004 ለሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መፍትሄ ለማፈላለግ ከተቋቋመው ኮሚቴ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ላለፉት አራት ወራት እጅግ ሰላማዊና ህገ መንግስታዊ በሆነ አግባብ አቤቱታችንን ለመንግስት ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ ጥያቄዎቻችን የሃይማኖት፣ የግለሰብና የማህበረሰብ ነጻነቶችን በተመለከተ በሕገ መንግስታችን የተቀመጡትን አቢይ መነሻዎች፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሁም መብቶችና ነጻነቶችን መሰረት ያደረጉ ህጋዊ የህዝበ ሙስሊሙ ብሶቶች ናቸው፡፡ ጥያቄያችንን ያቀረብነው በህገ መንግስቱ መግቢያ ላይ እንደሰፈረው “ባህሎችና ሃይማኖቶች ካለ አንዳች ልዩነት እንዲራመዱ የማድረ...ጉ አስፈላጊነት ጽኑ እምነታችን” በመሆኑ ነው፡፡ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. መንግስትም ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት የማረም ህገ መንግስታዊ ሀላፊነት እንዳለበት ተስፋ በማድረጋችን ነው፡፡ ጥያቄያችን ሕገ መንግስቱ ይከበር፣ ሃይማኖት በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱሕገ ወጥ እንደመሆኑ ሁሉ መንግስትም በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ስልጣንስሌለለው በዚህ ረገድ ባለስልጣናቱንና መዋቅሩን ይቆጣጠር የሚል መንፈስ ያስተጋቡ ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ሕገ-መንግስቱን የሚያከብርና የሚያስከብር የራሱንም መተዳደሪያ ደንብ የሚያከብር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትቢዋቀር ኖሮ እኛም ህዝባዊ ጥያቄ በመያዝ የመንግስት ቢሮዎችን ማንኳኳት ባላስፈለገን ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እነዳለ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የህዝባዊ ንቅናቄውን ቀና መነሻና ጥያቄ ለሀገርም ለህዝብም በማይፈይድ መንፈስና ገለጻ ማቅረቡ አሳዝኖናል፡፡ እንደሚታወቀው የካቲት 26፣ 2004 የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሰጠው ምላሽ ውስን የመርህም ሆነ የአፈጻጸም ግልጽነት ያልተስተዋለበት ከመሆኑ ባሻገር መጅሊሱ ሆን ብሎ ሲሰጣቸው የነበሩ መግለጫዎች ህዝባዊ ቁጣበማስከተላቸው የጥያቄያችን ይሰማ ትግላችንን ለመቀጠል መገደዳችን ይታወሳል፡፡ ይሁንና በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ምንም እንኳ ጥያቄአችንን በቀጥታ መልሰውልናል የሚል እምነት ባይኖረንም መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ እንደማይገባ ዳግም አረጋግጠውልናል፡፡ ተግባራዊነቱን በሂደት የምንታዘበው ጉዳይ ነው፡፡ ወትሮውንም የአፈጻጸም ስህተት እንጂ የመርህ ብዥታ እንደሌለ እውን ነው፡፡ በተጨማሪም የሃይማኖታችንን ኢትዮጵያዊ ሚናና ሕልውና የሚመለከቱ አንኳር ገጽታዎች እንዳሉ ብናምንም በህዝብ ለተወከልንበት ጥያቄዎች ከመርህ አኳያ ምላሽ የተሰጠበትክስተትና ተግባራዊ ፍንጭም በመስተዋሉ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያልተመረጠ አመራርም ሲጥሰው የቆየውን መተዳደሪያ ደንቡን መርምሮ ራሱን ከሀላፊነት ለማግለል በመወሰኑ ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳው ጥያቄ ምላሽ የማግኘት ሂደት ላይ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ የስልጣን ሽግግሩ ህዝባዊነት በሌለውና የመጅሊሱ መዋቅር አካልና አጋር ለሆነው እንዲሁም መዋቅራዊአቅም ለሌለው የኡለማዎች ምክር ቤት መሰጠቱ አግባብ እንዳልሆነም ይሰማናል፡፡ ቢሆንም ሕዝበ ሙስሊሙ በቅርቡ ለሚደረገው የመጅሊስ ምርጫ ይሆኑኛል የሚላቸውን ተወካዮች ለመምረጥ ብርቱ ዝግጅት ከማድረግ በተጨማሪ ከኮሚቴው ጎን በመሆን አፈጻጸሙ ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ግልጽና ፍትሃዊ መሆኑን በንቃትእንዲከታተልም ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በመላ ሀገሪቱ ያለው ህዝባዊ ጥያቄ ተመሳሳይ በመሆኑ መንግስት ካነሳነው ጥያቄ ጋር በተያያዘ ምክንያት ለእስር የተዳረጉ እንዲፈቱ፤ ማስፈራራቶችና የኃይል እርምጃዎች እንዲቆሙ ያደርግ ዘንድ አቤቱታችንን እናቀርባለን፡፡ ዴሞክራሲና እውነተኛ ሰላም ከማንም በላይለህዝበ ሙስሊሙ ብቸኛ የድል መስመሮች መሆናቸውን ድምጻችንን ለተጋሩ ሁሉ በድጋሚ እያሳሰብን ወደ ብጥብጥ ሊያስገቡየሚችሉ ድርጊቶች በመስጊዶችም ሆነ በማንኛውም ቦታ እንዳይከሰቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ በአላህ ስም እንጠይቃለን፡፡

12th Annual Badr Ethiopia Convention
July 5th to July 8th, 2012 
Houston,TX U.S.A 

Press release from Ethiopian American living in State of Washington

 Oromifa                                                                 Amharic

የበድር ኢትዮጵያ መግለጫ

Badr Communique'

EID MUBARAK

እንኳን ለዒድ -አል -ፊጥር አደረሳችሁ

ኢማስ ለእርሶና ለቤተሰቦ መልካሙን የኢድ አል ፈጥርን  በአል እየተመኘ ኢዱ በሚከበርበት ቀን በአዲሱ መስጂዳችን ከዙሁር ሰላት በኋላ  ከመላው ቤተሰቦ ጋእ መጥተው የደስታችን ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ጋብዘኖታል።

በአመት አንዴ ለሚመጣው ደስታ ውሎዎ ከኛ ጋር ይሁን! በድጋሚ ኢድ ሙባረክ!!!

አድራሻችን

3730 S. 166 st.

Seatac,WA 98188

Wishing you and your family the best Eid , we will celebrate EID at the same day at our NEW Mesjed after ZUHER prayer, insshallah you  All are invited please join and celebrate with us This joyous day that only comes to us once a year!

3730 S. 166th st.
Seatac, WA 98188
   

  

ለአንድ አፍታ ከወጣት አህመድ ግጥሞች  ጋር

Great links useful during this holy month of Ramadan:

http://www.moslim.se/Al-quran/Listen.html

http://www.alrahma.tv/Pages/Online/Details.aspx?ID=8

http://www.youtube.com/watch?v=16tZG7BvdpE&feature=player_detailpage#t=17s

 
Badr Radio/ BBN

http://www.badrradio.com/

 

Visitors Counter

209583
TodayToday178
YesterdayYesterday378
This WeekThis Week2211
This MonthThis Month7185
All DaysAll Days209583

Calendar